ዳኞች ስራ ላይ ባሉ ህጎችና ፋይዳቸው ላይ የጽሁፍ ውጤቶችን ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ ዳኞች ስራ ላይ ባሉ ህጎችና ፋይዳቸው ላይ የጽሁፍ ውጤቶችን ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ Sunday, November 21, 2021 1863 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ዳኞች በስራ ላይ ባሉ ህጎችና ፋይዳቸው ላይ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የጽሑፍ ውጤቶችን ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ገለጹ፡፡ አቶ ሰለሞን አረዳ ይህን የገለጹት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት በሆኑት በክቡር አቶ ተስፋዬ ነዋይ “የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ሕጋዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ” በሚል ርዕስ የታተመ መጽሐፍ የምረቃና የትችት መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡ Read more
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት አነሳ የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት አነሳ Friday, October 22, 2021 2136 የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉን የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት ገለጸ፡፡ Read more
ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ ስርዓቱን አዘመነ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ ስርዓቱን አዘመነ Wednesday, October 20, 2021 2373 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ ስርዓቱን አዘምኗል፡፡ ፍርድ ቤቱ ማንኛውንም የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ በሚከፈለው ብር መጠን ሳይገድብ፣ ባለጉዳዮች ወደ ባንክ መሄድ እና ጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው ክፍያ መፈፀም የሚችሉበት የአሰራር ማሻሻያ አድርጓል፡፡ በዚህ የክፍያ አፈጻጸም ማሻሻያ ስርዓት፡- Read more
የ2014 አዲስ ዓመት ጅማሬን አስመልክቶ ከጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት ለፌደራል ፍ/ቤቶች ዳኞች የተላለፈ የምስጋና መግለጫ የ2014 አዲስ ዓመት ጅማሬን አስመልክቶ ከጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት ለፌደራል ፍ/ቤቶች ዳኞች የተላለፈ የምስጋና መግለጫ Friday, September 10, 2021 2686 ክቡራንና ክቡራት ዳኞች ያጠናቀቅነው የ2013 ዓ.ም በፍርድ ቤታችን ጉልህ የሚባሉ የማሻሻያ ሥራዎች የተከናወኑበትና በዚህ ረገድ በቀጣይ ለሚመዘገቡ ስኬቶች መሠረት የተጣለበት ሆኖ የሚወሰድ ነው፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ለፍርድ ቤቱ የማሻሻያ ሥራ መሠረታዊ ከሆኑት እና በፍርድ ቤቶች የዳኞችን እና ተቋማዊ ነጻነትን፣ ገለልተኝነትን እንዲሁም ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል የተሻሻሉት የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ እና የፌደራል የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፀድቀው ወደሥራ መግባታቸው ጉልህ ሥፍራ የሚሰጠው ነው፡፡ እነዚህን አዋጆች ተግባራዊ ለማድረግም በርካታ ደንቦችና መመሪያዎች እየተዘጋጁና እየጸደቁ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ መካከል የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ እና የዳኞች ሥነምግባር እና የዲሲፒሊን ሥነሥርዓት ደንብ የፀደቁ ሲሆኑ በቅርቡ ፀድቀው ወደትግበራ እንደሚገቡ ከሚጠበቁት መካከል የአስተዳደር ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ እና የዳኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና መመሪያ ይጠቀሳሉ፡፡ Read more
በፍርድ ቤቱ ለፍትሃ ብሔር ገዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ አተገባበር ምቹ ሁኔታ ያለ መሆኑ ተገለጸ በፍርድ ቤቱ ለፍትሃ ብሔር ገዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ አተገባበር ምቹ ሁኔታ ያለ መሆኑ ተገለጸ Tuesday, August 31, 2021 2381 በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር አስተባባሪ ዳይሬክቶሬት በፍርድ ቤቱ የፍትሃ ብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመተግበር ምቹ አስቻይ ሁኔታ ያለ መሆኑን ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት ማረጋገጡን ገለጸ:: Read more
በፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ላይ ለዳኝነት ዘርፉ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ በፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ላይ ለዳኝነት ዘርፉ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ Sunday, August 22, 2021 2290 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዳኝነት ዘርፉ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላላቸው ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በፍትሐብሔርጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ላይ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ነሐሴ 15 ቀን 2013 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ፡፡ በሥልጠናው የተሳተፉት ብዛታቸው 65 የሆኑ የፍርድ ቤቱ ረዳት ዳኞች፣ ሴክሬታሪዎች፣ የችሎት ፀሐፊዎች፣ ሬጅስትራሮች እና ዳታ ኢንኮደሮች ናቸው፡፡ Read more
የፌደራል ዳኞች የሥነምግባር እና የዲሲፒሊን ክስ ሥነሥርዓት ደንብ ዓለም አቀፋዊ የዳኝነት መርሆዎችን መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ የፌደራል ዳኞች የሥነምግባር እና የዲሲፒሊን ክስ ሥነሥርዓት ደንብ ዓለም አቀፋዊ የዳኝነት መርሆዎችን መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ Sunday, August 22, 2021 2681 የፌደራል ዳኞች የሥነምግባር እና የዲሲፒሊን ክስ ሥነሥርዓት ደንብ ዓለም አቀፋዊ የዳኝነት መርሆዎችን እንዲሁም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥትን እና ሌሎች የአገሪቱን ሕጎች መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ረቂቅ ደንቡ ሲዘጋጅ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ዓለም አቀፍ የሕግ አማካሪ የሆኑት አሜሪካዊው ሚስተር ማይክል ከኒፍ ገለጹ፡፡ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሪፎርም አካል በሆነውና ማሻሻያ ተደርጎበት በቅርቡ በዳኝነት አስተዳደር ጉባኤ በጸደቀው የፌደራል ዳኞች የሥነምግባር እና የዲሲፒሊን ክስ ሥነሥርዓት ደንብ ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ከነሐሴ 15-25 ቀን 2013 ዓ.ም በአምስት ዙሮች በመሰጠት ላይ ነው፡፡ Read more
በፍርድ ቤቱ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው በፍርድ ቤቱ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው Sunday, August 15, 2021 2136 በቅርቡ የፀደቀውን የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ በ2014 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊው ቅድመ-ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 008/2013ን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ለማስተዋወቅና ትግበራውን ለማስጀመር ነሐሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም በራዲሰን ብሉ ሆቴል ውይይት ተካሒዷል፡፡ Read more