የአዋጅ መሻሻልን ተከትሎ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የችሎት አደረጃጀትና የዳኞች አሰያየም ላይ ትኩረት ያደረገ ጥናት ለተጨማሪ ግዓብት ለውይይት ቀረበ

2762

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 እና ሌሎች ተከታታይ የአዋጁ ማሻሻያዎችን በመሻር በጥር ወር 2013 ዓ.ም  በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጸደቀው አዲስ አዋጅ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐ ብሔር ስረ-ነገር ሥልጣን ላይ ለውጥ ማድረጉን ተከትሎ በፌዴራል መጀመሪያ ድረጃ ፍርድ ቤት ሊኖር ስለሚችል የችሎት አደረጃጀት እና የዳኞች አሰያየምን ለማመላከት የተካሄደ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ለፍ/ቤቱ አስተባባሪ ዳኞች፤ ዳኞች፣ ለሬጂስትራሮችና ለልዩ ልዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ለአስተያየት ቀረበ፡፡

የፌዴራል ፍ/ቤቶች ከፍተኛ አመራር እንዲያጸድቅ በቀረቡለት ሁለት ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ተወያየ

2705

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶችና ም/ፕዝደንቶች ሚያዚያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ እንዲያጸድቃቸው በቀረቡለት የፍትሃብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ረቂቅ መመሪያ እና የተሸሻለውን የCCMS (Court Case Management System) ለመተግበር የሚያስችል የስራ መዘርዝር እና ፍሰት የሚገልጽ ሰነድ ላይ ተወያየ፡፡

የስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት አማካሪ ድርጅት ዕቅድ ዝግጅቱ ያለበትን የስራ ደረጃ ለዐብይ ኮሚቴው ገለጸ

2570

የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን 3ኛ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ለማዘጋጀት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቀጠረው ጥምር አማካሪ ድርጅት በጽንሰ ጥናት ሪፖርቱ ባስቀመጠው የድርጊት መርሃ ግብር መሰረት የዕቅድ ዝግጅት ስራው ያለበትን ደረጃ በፍርድ ቤቱ በኩል ስራውን እንዲከታተልና አስፈላጊ ግብአቶችን እንዲያቀርብ ሃላፊነት ለተሰጣቸው ዐብይ እና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ዛሬ ሚያዚያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ገለጸ፡፡

በጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳዮችን እንዲመለከቱ ለተደራጁ ልዩ ችሎቶች የስራ አቅጣጫ ተሰጠ

2390

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የሚታዩባቸው ችሎቶች በጠቅላይ ፍ/ቤት መደራጀታቸውን አፈጻጸማቸውን በተመለከተ ለፕሬዝደንት ጽ/ቤትና ለሬዲስትራሮች የስራ አቅጣጫ ሰጡ፡፡ 

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ2012 በጀት ዓመት መልካም አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዳኞች እና ምድብ ችሎቶች እውቅና ሰጠ፡፡

2560

ፍርድ ቤቱ ከእያንዳንዱ ምድብ ችሎቶት በባህሪና በመዝገብ አፈጻጸም መልካም ውጤት ያስመዘገበ 1 ዳኛ በመምረጥ በአጠቃላይ ለ11 ዳኞች የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡

ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስችል ድጋፍ ተደረገለት

2516

ጥቅምት 5/2013 ዓ.ም የኢትጵያ የሕግ ባለሞያዎች ማህበር ለፌ/መ/ደ/ፈ/ቤት ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስችል የተለያዩ የጥንቃቄ ግብአቶች (Personal Protective Equipment) በድጋፍ መልኩ አበርክቷል፡፡

ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አመኔታ እንዲያገኙ ዳኞች በዘርፉ ላሉ የሥነምግባር መርሆዎች ተገዢ ሊሆኑ እንደሚገባ ተገለጸ

2492

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በአገልግሎት አሰጣጣቸው የሕዝብ አመኔታ ሊያተርፉ የሚችሉት ሥራቸውን የዳኝነት የሥነምግባር ደንቡን እና ዓለም አቀፍ የዳኝነት የሥነምግባር መርሆዎችን መሠረት አድርገው ሲያከናውኑ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የፍ/ቤቱን ሴት ሰራተኞች ማብቃትና ሃላፊነታቸዉን በብቃት መወጣት የሚያስችሉ ድጋፎችን ማመቻቸት እንዲሁም ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር አስፈላጊነት ተጠቆመ፡፡

3116

የፍ/ቤቱን ሴት ሰራተኞች ማብቃትና ሃላፊነታቸዉን በብቃት መወጣት የሚያስችሉ ድጋፎችን ማመቻቸት እንዲሁም ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር አስፈላጊነት ተጠቆመ፡፡

 

First3031323334353638