የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬደዋ ምድብ ችሎት የቢሮ እድሳት የምርቃት ስነ-ስርዓት ተካሄደ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬደዋ ምድብ ችሎት የቢሮ እድሳት የምርቃት ስነ-ስርዓት ተካሄደ Tuesday, July 30, 2024 283 ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬደዋ ምድብ ችሎት የቢሮ እድሳት የምርቃት ስነ-ስርዓት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ፣ የፌፌራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የበላይ አመራሮች፣ የህዝብ ተመካዮች የህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ኢሳ ቦሩ፣ የህዝብ ተወካዮች የፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ የተከበሩ አቶ ወንደሰን፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጀዋር፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የምክር ቤት አባላትና ስራ አስፈጻሚዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ተጋባዥ አንግዶችና የፍርድ ቤቱ ሰራተኞች በተገኙበት ተካሄደ፡፡ Read more
ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተከላካይ ጠበቆች ፣ረዳት ዳኞች እና ሬጂስትራሮች ስልጠና ተሰጠ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተከላካይ ጠበቆች ፣ረዳት ዳኞች እና ሬጂስትራሮች ስልጠና ተሰጠ Monday, July 22, 2024 284 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከላካይ ጠበቆች ፣ ረዳት ዳኞች እና ሬጂስትራሮች “ Work Related Stress Management” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ሐምሌ 9 እና 11 ቀን 2016 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአፍሪካ ህብረት በህጻናት ጥበቃ ጉዳዮች እና ሌሎች ጎጂ ተግባራት በኢትዮጵያ ሀገራዊ የክትትል ተልዕኮ ወርክሾፕ ላይ በመገኘት ሪፖርት አቀረበ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአፍሪካ ህብረት በህጻናት ጥበቃ ጉዳዮች እና ሌሎች ጎጂ ተግባራት በኢትዮጵያ ሀገራዊ የክትትል ተልዕኮ ወርክሾፕ ላይ በመገኘት ሪፖርት አቀረበ Thursday, July 18, 2024 439 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት "African Union Country Monitoring Mission/Workshop on Child Protection issues and other Harmful Practices in Ethiopia"በሚል የተዘጋጀ 3 ቀን ወርክሾፕ ላይ በመገኘት ፍርድ ቤቶች በህጻናት መብት እና ደህንነት ዙሪያ ያከናወኗቸው ስራዎች ላይ ገለጻ አድርጓል፡፡ Read more
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ክትትልና ግምገማ ተካሄደ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ክትትልና ግምገማ ተካሄደ Friday, July 12, 2024 307 የፌደራል ፍርድ ቤቶችን በዋይድ ኤርያ ኔትወርክ (WAN) ለማገናኘት እየተከናወነ የሚገኘውን የፕሮጀክት አፈጻጸም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፕላንና በጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ የኢትዮ ቴሌኮም የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃና ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲሁም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጎብኝተዋል፡፡ Read more
በተከታታይ የወንጀል ክስ አሰማም ሂደት ዙሪያ በተዘጋጀ ጥናት ላይ የማረጋገጫ እና የውይይት መድረክ (Validation and Consultation Workshop) ተካሔደ በተከታታይ የወንጀል ክስ አሰማም ሂደት ዙሪያ በተዘጋጀ ጥናት ላይ የማረጋገጫ እና የውይይት መድረክ (Validation and Consultation Workshop) ተካሔደ Monday, July 8, 2024 557 ከፌደራል ፍርድ ቤቶች፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከፌደራልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር እና ከፌደራል ጠበቆች ማሕበር የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች፣ ዳኞች እንዲሁም ባለሙያዎች የተሳተፉበትና በተከታታይ የወንጀል ክስ አሰማም ሂደት (Continuous Criminal Trial) ላይ ‹‹Assessment of gaps that obstruct continuous ctriminal trials in federal courts›› በሚል ርዕስ በተከናወነ ጥናት ላይ የማረጋገጫ እና የምክክር መድረክ (Validation Workshop) ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሄዷል፡፡ Read more
ፍርድ ቤቱ የሰበር ዉሳኔ የድምጽ ቅጂ ለኢትዮጵያ ዓይነ ስዉራን ብሔራዊ ማህበር አበረከተ ፍርድ ቤቱ የሰበር ዉሳኔ የድምጽ ቅጂ ለኢትዮጵያ ዓይነ ስዉራን ብሔራዊ ማህበር አበረከተ Wednesday, July 3, 2024 367 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠባቸዉን በድምጽ ቅጂ መልክ የተዘጋጁ ከቅጽ 1-18 ያሉ የሰበር ዉሳኔዎች ለኢትዮጵያ ዓይነ ስዉራን ብሄራዊ ማህበር ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ/ም አበረከተ። Read more
ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችና የስራ ሃላፊዎች የ‹‹stress management›› & ‹‹ emotional intelligence›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ የክህሎት ስልጠና ተሰጠ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችና የስራ ሃላፊዎች የ‹‹stress management›› & ‹‹ emotional intelligence›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ የክህሎት ስልጠና ተሰጠ Monday, July 1, 2024 320 ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችና የስራ ሃላፊዎች በቀን 22/10/2016 ዓ.ም ‹‹stress management›› & ‹‹ emotional intelligence›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የስልጠናው አላማ ዳኞችና የፍርድ ቤት የስራ ሃላፊዎች ከዕለት ተዕለት ስራቸው ጋር በተገናኘ ጫናዎችን የሚያስተናግዱበት፣ የሚቋቋሙበትንና የአመራር ክህሎትን የሚያሳድጉባቸው ክህሎቶች/ዘዴዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨባጫ መስጠት ነው። Read more
በሩሲያ ፌዴሬሽን የሕገመንግስት ፍርድ ቤት በተዘጋጀውና ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ25 በላይ ሃገራት ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶች በተገኙበት ‹‹Protection of Rights and Constitutional Supervision›› በሚል ርዕስ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ ተካሂዷል በሩሲያ ፌዴሬሽን የሕገመንግስት ፍርድ ቤት በተዘጋጀውና ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ25 በላይ ሃገራት ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶች በተገኙበት ‹‹Protection of Rights and Constitutional Supervision›› በሚል ርዕስ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ ተካሂዷል Thursday, June 27, 2024 301 በሩሲያ ፌዴሬሽን የሕገመንግስት ፍርድ ቤት ‹‹Protection of Rights and Constitutional Supervision›› በሚል ርዕስ በቀን 19/10/2016 ዓ.ም በተዘጋጀውና ከ25 በላይ ሃገራት ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶች በተገኙበት ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ ላይ የኢፌዲሪ የሕገመንግሥት አጣሪ ጉባኤ ሰብሳቢና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በሩሲያ ፌዴሬሽን በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ሕገመንግሥታዊ ፍርድ ቤት በመገኘት የኢፌድሪ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤን ሚና፣ አወቃቀር፣ አደረጃጀትና አሠራር፣ ሥልጣንና ተግባራቱን በተመለከተ ያለውን ተሞክሮ አቅርበዋል Read more