ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጾታዊ ጥቃት ነጻ የሆነ ማህበረሰብ የመገንባት ዓላማ ያለው መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ገለጹ፡፡
«ጾታን መሰረት አድርገዉ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ከመከላከል አንጻር የአመራሮች ሚና» በሚል ርዕስ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች አመራሮችና ሰብሳቢ ዳኞች በቢሾፍቱ ከተማ አዱላላ ሪዞርትና ስፓ ታሕሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም የተዘጋጀ የስልጠና መርሐ-ግብር ተሒዷል፡፡