የፌደራል ፍትህ አካላት የወንጀል ፍትህ አስተዳደር አብይ ኮሚቴ የውይይት መድረክ ተካሄደ

345

የፌደራል ፍትህ አካላት የወንጀል ፍትህ አስተዳደር አብይ ኮሚቴ የውይይት መድረክ ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ስርአት ውስጥ ከአሰራርና ከህግ ረገድ የሚስተዋሉ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ውይይት ተካሂዷል

የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/13 እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሄደ

380

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር .1233/13 እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13ን ለማሻሻል የሚያስችል የግብዓት ማሰባሰብ የውይይት መድረክ ከዉጭ ባለድርሻ አካላት ጋር ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ/ም አከናዉኗል

የፌዴራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/13 እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13ን ለማሻሻል የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተዘጋጀ

393

የፌዴራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/13 እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13ን ለማሻሻል የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በጀስቲስ ፎር ኦል ኘሪስን ፌሎሺፕ ትብብር በቀን 17/09/2016 ዓ.ም የሶስቱም ደረጃ ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ተጠሪ ዳኞች፤ ሰብሳቢ ዳኞች እና የስራ ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት ተደርጓል::

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የእርስ በእርስ የዉይይት መድረክ በይፋ ተከፈተ

402

ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የእርስ በርስ የዉይይት መድረክ ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል

ዉይይቱ ለአንድ ዓመት የታቀደና በየወሩ አንድ ጊዜ የሚደረግ ሲሆን ፍርድ ቤት በህዝብ ዘንድ አመኔታን ያተረፈ እንዲሆን እና ወጥነት ያለዉ ዉሳኔ በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ለመወሰን የሚያስችል ወሳኝ ጉዳዬች ላይ ትኩረት አድርጎ ዳኞች እርስ በእርስ እንዲወያዩ የሚያስችል ነው::

“ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡ ህጻናት ልጆቻችን ናቸው ፍላጎታቸውን እና መብቶቻቸውን ልናከብርላቸው ይገባል”

338

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከUNFPA ጋር በመተባበር ከሶስቱም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ሬጅስትራሮች፣ ችሎት ፀሀፊዎች እና ችሎት ስነሰርዓት ሰራተኞች ባዘጋጀው በህጻናት ተግባቦት እና አያያዝ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ 

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር እና የዳኝነት ዘርፍ ዕቅድ አፈጻጸም እንዲሁም የአውሮፖ ህብረት ወንጀል ፍትህ አስተዳደር ማሻሻያ ፕሮጀክት አመታዊ ሪፖረት ላይ ከግንቦት 9 ቀን እስከ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት ተካሔደ

323

የአስተዳደር ዘርፍ ዕቅድ አፈጻጸም መድረኩን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት መድረኩ የተከናወኑ ስራዎችን ለመለየት፣ ያልተከናወኑ ተግባራትን ደግሞ እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ እንዴት መፈጸም እንዳለባቸው ለመወያየት፣ እንዲሁም በፍ/ቤቱ አውሮፓ ህብረት የወንጀል ፍትህ ማሻሻያ ፕሮጀክት አፈጻጸም በሁሉም ፍ/ቤቶች ምን ይመስላል፣ ምን ስራዎች ተከናወኑ፣ ምን ይቀራል በሚለው ላይ በመወያየት ግብዓት በማሰባሰብ የፍ/ቤቱ አሰራሮች በማሻሻል ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥበት ተቋም ለመገንባት የሚረዳ መሆኑን እንዲሁም ቀሪ ስራዎች እንዴት ይፈጸማሉ በሚለው ላይ የሀሳብ ልውውጥ ለማድረግ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል

ለ45 ተከላካይ ጠበቆች 2ኛ ዙር የ6 ቀን አቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

361

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት እና በፌዴራል የሕግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ትብብር በተመረጡ በፀረ-ሽብር አዋጅ ፣ በተከላካይ ጠበቃ ሙያ ስነምግባር እና በተመረጡ የወንጀል ገዳዮች ከግንቦት 5 - 10 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ የ6 ቀናት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በስልጠናዉ 45 ተከላካይ ጠበቆች የሚሳተፉ ሲሆን በእያንዳንዳቸው የስልጠና ርዕሶች ሰፊ ልምድ ያላቸዉ 3 አሰልጣኞች ስልጠናዉን የሚሰጡ ይሆናል። ስልጠናው የሰልጣኞችን እዉቀትና ክህሎት ለማሳደግ ትልቅ ጠቀሜታ ያለዉ ሲሆን የሚያገለግሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች በብቃት ፣ በትጋት ፣ በጥራት እና በተጠያቂነት ስሜት እንዲያገለግሉ አመለካከቻቸዉን ጭምር ያግዛቸዋል ተብሎ የታመነበት ስልጠና ነዉ።

የህጻናት ተስማሚ ፍትህ ሞጁል ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ

607

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከ UNICEF ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የህጻናት ተስማሚ ፍትህ ሞጁል ላይ ከተለያዩ ክልሎች እና ከፌደራል ፍ/ቤት ለተወጣጡ ዳኞች እና ባለሙያዎች ለሶስት ቀናት የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

123468910Last