የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ሰራተኞች የድልድል መመሪያ ላይ ለድልድልና ቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ አባላት ገለጻ ተደረገ

494

በ2015 ዓ.ም ጸድቆ በ2016 ዓ.ም በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በወጣው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ሰራተኞች ደንብ ቁጥር 1/2015 መሰረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ሰራተኞች ጉባኤ መቋቋሙ የሚታወስ ነው፡፡ ጉባኤው በደንቡ አንቀጽ 30(3) ድንጋጌ መሰረት አዲስ በተሰራው አደረጃጀት ሰራተኞችን ደልድሎ ለማሰራት የድልድል መመሪያ ያወጣ ሲሆን በዚሁ መመሪያ መሰረትም የድልድል ኮሚቴ እና የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡

ለ45 ተከላካይ ጠበቆች የ6 ቀን አቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

382

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት እና በፌዴራል የሕግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ትብብር በተመረጡ የወንጀል ጉዳዮች ፣ በፀረ-ሽብር ሕግ እና የተከላካይ ጠበቆች የሙያ ስነምግባር ላይ ባተኮሩ ጉዳዮች ከሚያዝያ 14 - 19 ቀን 2016 ዓ.ም ለ6 ቀናት የቆየ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ለ45 ተከላካይ ጠበቆች ተሰጠ።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ የዉይይት መድረክ ተጠናቀቀ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስተባባሪነት መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየዉ 6ኛው ዙር የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ የዉይይት መድረክ ተጠናቀቀ፡፡

420

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የጉባኤዉ ሰብሳቢና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ጉባኤዉ ትልቅ ስልጣን እና ኃላፊነት ያለዉ መሆኑን አንስተዉ አሁን ስራ ላይ ባለዉ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት የጉባኤዉ ስልጣን በፍርድ ቤት ነፃነት፣ተጠያቂነትና ከፍትህ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በመለየት የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ እንዲሁም አስፈላጊ ሆነዉ ሲገኝ ኣዳዲስ ህጎች እንዲወጡ ወይም ነባር ህጎች እንዲሻሻሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሃሳብ ማቅረብ፤ በአጠቃላይ የፍርድ ቤቶችን ዉጤታማነት ከፍተኛ የሚያደርጉ የማሻሻያ ሃሳቦችን ማዳበር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አለም አቀፍ ናርኮቲክ እና ሕግ ማስከበር ቢሮ ልኡክ ቡድን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽሕፈት ቤት ጉብኝት

413

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽሕፈት ቤት ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አለም አቀፍ ናርኮቲክ እና ሕግ ማስከበር ቢሮ (Department of State’s Bureau of International Narcotics and Law Enforcement (INL)) ከመጡ ልኡካን ጋር ሐሙስ መጋቢት 19/2016 የጽሕፈት ቤቱን አቅም በዘላቂነት መገንባት በሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አካሂዷል።

በረቂቅ የህፃናት ፍትህ የስልጠና ሞጁል ላይ የግብአት ማሰባሰቢያ ዉይይት ተደረገ

617

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከዩኒሴፍ (UNICEF) ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉን የህፃናት ፍትህ የስልጠና ሞጁል ላይ የግብዓት ማሰባሰቢያ ዉይይት መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም አድርጓል፡፡

ፍርድ ቤቱ አዲስ ከተሾሙ ዳኞች ጋር የስራ ማስጀመሪያ እና የትዉዉቅ ፕሮግራም አደረገ

578

 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዲስ ከተሾሙ የፍርድ ቤቱ ዳኞች ጋር መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም የስራ ማስጀመሪያ እና የትዉዉቅ ፕሮግራም አድርጓል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስራ ሃላፊዎች የፕሮጀክት አስተዳደር ስልጠና

687

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የፍትሕ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች ከአውሮፓ ህብረት የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ማሻሻያ ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የፕሮጀክት አስተዳደር የ5 ቀን ስልጠና ወስደዋል፡፡

በህፃናት የቀለብ አወሳሰን ረቂቅ መመሪያ ላይ ዉይይት ተደረገ

542

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ፅ/ቤት ባዘጋጀዉ የህፃናት ቀለብ አወሳሰን ረቂቅ መመሪያ ላይ የግብአት ማሰባሰብያ ዉይይት አድርጓል፡፡ 

First2345791011Last