የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ለመተግበር ያስችለው ዘንድ የተከማቹ መዛግብትን በቅድሚያ ማጥራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጾ ጊዜያዊ ዳኞች እንዲመደቡለት ያቀረበውን ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ይህንን ተከትሎ ጉባዔው በፌዴራል ዳኝት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 26 (2) ከአንድ ፍርድ ቤት ወደ ሌላ የፍርድ ቤት ደረጃ በጊዜያዊነት ዳኞችን መድቦ የማሰራት ስልጣኑን ተጠቅሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሸክምን ይወጣሉ ያላቸውን አራት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ የመዝገብ ክምችት እንዲያጠሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡