በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተቀናጀ የጉዳዮች አስተዳደር መረጃ ስርዓት (ICMIS) እና ኤሌክትሮኒክ-ሰነድ አስተዳደር ስርዓት (e-RMS) ልማትና ትግበራ ጽንሰ-ተልዕኮ (Inception Mission) መርሃ ግብር ተካሄደ

290

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሚሰጠውን የዳኝነት አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ ራስ-ተግባሪ (Automation) ስርዓት የተደገፈ ለማድረግ የወጠነው ፐሮጀክት በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት- ፍትህ ተግባራት ኢትዮጵያ (USAID- Justice Activities-Ethiopia) ድጋፍ ስርዓቱን ለማልማት በአለም ዓቀፍ ጨረታ ያሸነፈው ሲነርጂ ኢንተርናሽና ሲስተምስ የተባለ ድርጅት ጽንሰ-ተልዕኮ መርሃ ግብር (Inception Mission Schedule ) ከግንቦት 1 -5 ቀን 2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሙስና ተግባራት መከላከያና መቆጣጠሪያ ስትራቴጂ ይፋ አደረገ

310

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያዘጋጀውን እና በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ውይይት ተደርጎበትና ቅቡልነት አግኝቶ ለትግበራ ዝግጁ የሆነውን “በዳኝነት አካል ውስጥ የሚታዩ የሙስና ተግባራት መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ስትራቴጂ” የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ የምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኞች፣ ሰብሳቢ ዳኞች፣ የዳኞች ተወካዮች እና የአስተዳደር ዘርፍ ልዩ ልዩ የስራ ክፍል ሃላፊዎች በተሳተፉበት የውይይት መድረክ ይፋ አድርጓል፡፡

ስትራቴጂው ይፋ የተደረገበት የውይይት መድረክ ለስትራቴጂው አተገባበር የሚገጁ ሃሳቦችን በማንሸራሸር ይሁንታ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የተገልጋዮች የእርካታ ደረጃ በአማካይ 78 በመቶ መሆኑን ጥናት አመለከተ

301

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ተገልጋዮች በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያላቸውን የእርካታ ደረጃ ለማወቅ በገለልተኛ ተቋም በተካሔደ የጥናት ግኝት በአማካይ 78 በመቶ የሚሆኑ ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጡ እርካታ እንዳላቸው መግለጻቸውን የጥናቱ ውጤት አመለከተ፡፡

ይህም ውጤት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ለተገልጋዮች የእርካታ መመዘኛ ነጥብ ከተቀመጠው 75 በመቶ በላይ የተመዘገበበት በመሆኑ ውጤታማ የሚባል የእርካታ ደረጃ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ፍርድ ቤቱ የዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎችን አቅም ለማጎልበት የሚያከናውነው ሥራ ትውልድን የማነጽ ተግባር እንደሆነ ተጠቆመ

286

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት ከሚገኙ የሕግ ትምሕርት ቤቶች ጋር በመቀናጀት የሕግ ተማሪዎች በፍርድ ቤቶች የሜንተርሽፕ እና የኢንተርንሽፕ ፕሮግራም እንዲሳተፉ በማድረግ የሚያከናውኑት ተግባር ትውልድን የማነጽ ሥራ መሆኑን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ ክቡር አቶ ተስፋዬ ንዋይ ገለጹ፡፡

ፍርድ ቤቱ የዲጂታል የሀብት ማስመዝገብ መርሐ-ግብር አስጀመረ

319

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የዲጂታል የሀብት ምዝገባና ማሳወቅ መርሐ-ግብር በፌደራል ፍርድ ቤቶች መጀመሩን መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ/ም በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ በተካሔደ ሥነሥርዓት ይፋ አደረጉ፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተግባራዊ የሚደረገውን የዲጂታል የሀብት ምዝገባና ማሳወቅ መርሐ-ግብር የተጀመረው ፍርድ ቤቱ እና የፌደራል የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በጋራ ባዘጋጁት ሥነሥርዓት ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ በተከናወነ ሥነሥርዓት ነው፡፡

የፍ/ቤቱ ዳኞች በጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር እና በመዛግብት አፈጻጸም ዙሪያ አበረታች ውጤት ማስመዝገባቸው ተገለጸ

ፍርድ ቤቱ 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከመንግስት ማግኘቱም ተጠቁሟል

363

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በ2014 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደርን ተግባራዊ በማድረግ እና በመዛግብት አፈጻጸም ያስመዘገቡት ውጤት አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው የፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ገለጹ፡፡

ክብርት ፕሬዚደንትዋ ይህን የገለጹት የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳኞች እና ረዳት ዳኞች በተሳተፉበትና በፌደራል ፍ/ቤቶች የአምስት ዓመታት (2014-2018 ዓ.ም) ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ዋና ዋና ይዘት እና በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የችሎቶችና ዳኞች የ2014 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የመዛግብት አፈጻጸም ላይ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል የተደረገውን ውይይት ሲያጠቃልሉ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በፓናል ውይይት አከበሩ

330

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ111ኛ ጊዜ፣ በአገራችን ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) የፌደራል ፍርድ ቤቶች የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በፓናል ውይይት አከበሩ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፓናል ውይይቱን በንግግር ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር የሴቶች የሲቪልም ሆነ የፖለቲካ መብት እና ተሳትፎ ከኢኮኖሚ መብት ጋር ተያያዥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ማሳያው የግል ገቢ የሌላት ሴት ከሚበድላት ባል ጋር ለመኖር እንደምትገደድና አማራጭ የሥራ ዕድል የሌላት ሴትም የመጥፎ አለቃን እብሪትና ትንኮሳ ችላ ለመኖር የምትገደድ መሆንዋ ትስስሩን እንደሚያሳይ አስረድተዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ውጤታማ የሚሆነው ከባለድርሻ አካላት እና ከሕብረተሰቡ አስፈላጊው ትብብር እና ድጋፍ ሲሠጠው መሆኑን ገለጹ

360

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሹመታቸውን ያጸደቀላቸው የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አመራሮች የቃለመሀላ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም አስፈጽመዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ስራ ውጤታማ የሚሆነው ከባለድርሻ አካላት እና ከሕብረተሰቡ አስፈላጊው ትብብርና ድጋፍ ሲሰጠው መሆኑን በቲውተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ክብርት ፕሬዝደንቷ ከምክክር ኮሚሽኑ ብዙ ይጠበቃልም ብለዋል::

First45679111213Last