በጥቅምት 2011 ዓ.ም. የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት እንድሆን የቀረበልኝን ጥያቄ ስቀበል ዋናው አጀንዳዬ ሕዝብ በፍርድ ቤቶች ላይ ያለው አመኔታ እንዲመለስ ማድረግ ነበር፡፡
ይህን አጀንዳ ለማሳካት መሰራት የነበረበት ስራ ስፋት ውስብስብነት ፈታኝ የነበረ ቢሆንም ግልፅ ግቦችን በማስቀመጥ፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ተግባራትን በመለየት፣ እና ይህን ለማሳካት የሚችል ጠንካራ የአመራር ቡድን እንዲኖር በማድረግ እዚህ ደርሰናል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን እያካሄድነው ያለነው የሪፎርም ስራ የመጀመሪያ ምዕራፍ በማጠናቀቅ የሁለተኛ ምዕራፍ ተግባራትን ጀምረናል፡፡ የሕዝብ አመኔታ መመለስም የአምስት አመት ስትራቴጂ የተቋሙ ራዕይ ሆኖ ተተክሏል፡፡
ዛሬ ይፋ የሚደረገው የተገልጋዮች እርካታ ጥናት በመጀመሪያው ምዕራፍ ባደረግነው ለውጥ ውስጥ ባከናወናቸው ተግባራት የመጣውን በጎ ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡ ................