የህጸናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር በፍርድ ቤት መር አስማሚነት እና የመስማማት ክህሎት ላይ 2ተኛ ዙር ስልጠና ተሰጠ

303

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከUNFPA እና Save The Children International ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የህጻናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር በፍርድ ቤት መር አስማሚነት እና የማስማማት ክህሎት ላይ ለዳኞች ፤ረዳት ዳኞች እና የሶሻል ወርክ ባለሙያዎች የካቲት 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም 2ተኛ ዙር ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በወንጀል ነክ ድርጊት ዉስጥ ገብተዉ ከተገኙ ህጻናት እንዲሁም በሴቶች እና ህጻናት ችሎት ለሚሰሩ የፌዴራል ዳኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

1860

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በወንጀል ነክ ድርጊት ዉስጥ ገብተዉ ከተገኙ ህጻናት እንዲሁም በሴቶች እና ህጻናት ችሎት ለሚሰሩ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰኔ 14 እና 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮሚቴ አማካኝነት እየተዘጋጀ ባለው General Comment 27 on Access to Justice for children ላይ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተካሄደ

2012

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናትና ፍትህ ፕሮጀክት በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮሚቴ አማካኝነት እየተዘጋጀ ባለው General Comment 27 on Access to Justice for children የሃገራችን ህጻናት አስተያየት ለማካተት በማሰብ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከአዲስ አበባ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና የህጻናት ፓርላማ የተውጣጡ ህጻናትን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማሰባሰብ ግብዓት ተቀብሏል፡፡

ፍርድ ቤቱ የህጻናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያና የዳኞች ለህጻናት ተስማሚ ፍትህ የስልጠና ማንዋልን አስመረቀ

2977

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የህጻናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያና የዳኞች ለህፃናት ተስማሚ ፍትህ የስልጠና ማንዋልን ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም አስመርቋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአፍሪካ ህብረት በህጻናት ጥበቃ ጉዳዮች እና ሌሎች ጎጂ ተግባራት በኢትዮጵያ ሀገራዊ የክትትል ተልዕኮ ወርክሾፕ ላይ በመገኘት ሪፖርት አቀረበ

2654

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት "African Union Country Monitoring Mission/Workshop on Child Protection issues and other Harmful Practices in Ethiopia"በሚል የተዘጋጀ 3 ቀን ወርክሾፕ ላይ በመገኘት ፍርድ ቤቶች በህጻናት መብት እና ደህንነት ዙሪያ ያከናወኗቸው ስራዎች ላይ ገለጻ አድርጓል፡፡

በህጻናት ዝቅተኛ የወንጀል ተጠያቂነት እድሜ ላይ ያተኮረ ስልጠና እና ውይይት ከኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ተካሄደ

2515

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት እና በUNFPA ትብብር የህጻናት የወንጀል ተጠያቂነት ዝቅተኛ እድሜን በተመለከተ ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከክቡራን የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት ተደርጓል

በረቂቅ የህፃናት ፍትህ የስልጠና ሞጁል ላይ የግብአት ማሰባሰቢያ ዉይይት ተደረገ

2698

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከዩኒሴፍ (UNICEF) ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉን የህፃናት ፍትህ የስልጠና ሞጁል ላይ የግብዓት ማሰባሰቢያ ዉይይት መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም አድርጓል፡፡

ወንጀል ነክ ነገር ዉስጥ ገብተዉ የተገኙ ወጣቶችና በሴቶችና ህጻናት ችሎት ያጋጠሙ መልካም ተሞክሮዎችና ተግዳሮቶች (Children in conflict with the law) በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ከፌደራልና ክልል ፍርድ ቤቶች ከተዉጣጡ ዳኞችና ማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

1830

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከዓለም አቀፉ የህጻናት አድን ድርጅት (Save The Children) ጋር በመተባበር ወንጀል ነክ ነገር ዉስጥ ገብተዉ የተገኙ ወጣቶችና በሴቶችና ህጻናት ችሎት ያጋጠሙ መልካም ተለሞክሮዎችና ተግዳሮቶች (Children in conflict with the law) በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የምክክር መድረክ 50 የሚጠጉ ከፌደራልና ክልል ፍርድ ቤቶች የተዉጣጡ ዳኞችና ማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

12