ህፃን ሒዳያ አማን መሀመድ እና አመተበል መሃመድ የሰ-መ-ቁ 185175
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 86183 በቀን 17/05/2011 ዓ/ም እንዲሁም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 2301172 በቀን 19/02/2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ ክርክሩ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረው የአሁን አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ ሲሆን የአሁን ተጠሪ 1ኛ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡የአመልካች ሞግዚት በቀን 14/06/2010 ዓ/ም ባቀረቡት ማመልከቻ የህፃን ሒዳያ አማን ወላጅ አባት በቀን 21/05/2010 ዓ/ም በሞት የተለዩ ሲሆን የወራሽነት ውሳኔ በማቅረብ የሟች የውርስ ሀብት እንዲጣራ የውርስ አጣሪ እንዲሾም ጠይቀዋል፡፡ፍ/ቤቱም የሟች ውርስ እንዲጣራ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ የአሁን ተጠሪ እና ሰነያ መሀመድ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ የውርስ አጣሪ ውርሱን አጣርቶ ሪፖርት እንዲያቀርብ ባዘዘው መሰረት በቀን 26/02/2011 ዓ/ም ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ግራቀኙም አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡በተለይም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-34360 ኦ.ሮ የሆነውን ተሽከርካሪ በተመለከተ የውርስ አጣሪ ባጣራው መሰረት የቀረበው ማስረጃ ተሽከርካሪው በሟች ስም የሚገኝ ቢሆንም ለ1ኛ ጣልቃገብ /የአሁን ተጠሪ/ተሽከርካው ሟችን ጨምሮ ቤተሰባቸውን እንዲረዳ እንዲሁም ለ1ኛ ጣልቃገብም ሀብት እንዲሆን የተገዛ ተሽከርካሪ እንደሆነና ገንዘቡንም ከአረብ ሀገራት በመሰራት ካገኘሁት ገቢ የተገዛ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በበኩላቸው ይህን ክደው ተከራክረዋል፡፡...........
15574