ሆሆተ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እናወ/ሮ ዘውዲቱ በዳሶ የሰ/መ/ቁ 256580
በከሳሽ የቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ ከአመልካች ፋብሪካ በሚወጣው መርዛማ ጭስ ምክንያት የግል ንብረቴ የሆነውን የሆላንድ ጥጃ ግምቱ ብር 10,000.00 (አስር ሺ) እና የሆላንድ የወተት ላም ብር 170,000.00 (አንድ መቶ ሰባ ሺህ) መስከረም 06 ቀን 2014 ዓ.ም ጥጃዋ ወዲያውኑ ስትሞት ላሚቷ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ሞታለች፡፡ስለሆነም የሆላንድ ላሟ ከነጥጃዋ የዋጋ ግምት በድምሩ ብር 180,000.00 (አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ) የሚያወጡ ሲሆን ላሟ ከመታመሟ በፊት በቀን 27 ሊትር ወተት የምትሰጥ ሲሆን የአንድ ሊትር ወተት ዋጋ ብር 40 የሚሸጥ በመሆኑ በቀን ብር 1080 (አንድ ሺህ ሰማኒያ) ሲሆን በወር ብር 32‚400 (ሰላሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ብር) ገቢ ሳገኝ የነበረ ሲሆን ላሟ ለሶስት ወር ከ 9 ቀናት ታማ ምርት በማቆም ስትታከም በነበረበት ያጣሁት ገቢ ብር 106,920.00 (አንድ መቶ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ) ጨምሮ በአጠቃላይ ብር 286 920.00 (ሁለት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ እንዲወሰንልኝ የሚል ነው፡፡ተጠሪም በሰጡት መልስ ፋብሪካው ሲቋቋም በአካባቢው ላይ ተጽዕኖ የማያደርስ ስለመሆኑ ተረጋግጦ ነው፣ የክርክር መነሻ የሆኑት ጥጃ የሞተችበት እና ላሚቷ የታመመችበት ጊዜ የአመልካች ፋብሪካ ስራ ያልጀመረ በመሆኑ ለላሞቹ ሞት ምክንያት የደረሰው ጉዳት ከፋብሪካው የወጣ ጭስ ሊሆን የማይችል በመሆኑ አመልካች ለተጠሪ ጥጃ እና ላም መሞት ኃላፊነት የለበትም፤ካሳ ለመክፈልም ሊገደድ አይችልም በሚል የቀረበው ክስ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…
3505
Documents to download
-
256580(.pdf, 1.05 MB) - 489 download(s)