መ/ር ምህረት መስፍን ቀረቡ እና አቶ ምስጌ ብርሃን የሰ/መ/ቁ252593
ጉዳዩ የመፋለም ክስን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስማዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በስር ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ተጠሪ በወገዳ ከተማ ቤትኖራ ቀበሌ የሚገኘውን 12 ሜትር በ 14 ሜትር የሆነውን የከተማ ይዞታና ቤት አያታቸው እማሆይ ዘውዲቱ አብተው በምሪት አግኝተው ለልጃቸው ወይም ለተጠሪ እናት ወ/ሮ እባቡ ካሴ በስጦታ የሰጧቸውና ይህንንም ይዞታ የተጠሪ እናት በመሞታቸው ተጠሪ በውርስ ያገኙት ሆኖ እያለ አመልካች በ 2009 ዓ.ም በሀሰት በከተማ ማዘጋጃ ቤት በማስጠናት ይዞታውን የያዙባቸው በመሆኑ ለቀው እንዲያስረክቧቸው እንዲሁም ወጪና ኪሳራ እንዲከፍሏቸው ክስ አቅርበዋል፡፡ አመልካች የካቲት 11 ቀን 2012 ዓ.ም የተፃፈ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና አማራጭ መልስ አቅርበዋል፡፡ የአማራጭ መልሳቸውም ይዘት አከራካሪውን ቦታ ጨምሮ 12 ሜትር በ 25 ሜትር የሆነውን ይዞታ ከ 1976 ዓ.ም ጀምሮ ይዘውት እየተገለገሉበት የሚገኝና በ2007 የይዞታ ማረጋገጫ ያወጡበት የራሳቸው ይዞታ በመሆኑ የቀረበው ክስ ውድቅ ሊሆን ይገባል በማለት መልሳቸውን አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…
1621
Documents to download
-
252593(.pdf, 846.65 KB) - 251 download(s)