ሲቀላ ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና ወ/ሮ አረግዋ ጠብቀው የሰበር መዝገብ ቁጥር - 247036
ጉዳዩ የተጀመረው በቀድሞ ደቡብ ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል መንግስት የአርባምንጭ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የስር ከሳሽ በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ዝርዝር ይዘቱ በአጭሩ ባለቤታቸው የ ፶ አለቃ እንግዳ ንጉሴ በህይወት በነበረበት ጊዜ በመለያ ቁጥር 207 የሚታወቅ 625 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ይዞታ ከወ/ሮ ተፈሪ ወልደጊዮርጊስ የገዙ መሆኑን በመሬቱ ላይ ግብር እስከ 2007 አ.ም ድረስ የተከፈለ ቢሆንም የይዞታ ባለቤትነት ወደ አመልካች እና ሌሎች ወራሾች ስም እንዲዞርላቸው ያቀረብነው ጥያቄ ተከሳሽ ፍቃደኛ ባለመሆኑ የባለቤትነት ስም ወደ ከሳሽ ስም እንዲያዞር እንዲወሰን የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…
3042
Documents to download
-
247036(.pdf, 853.88 KB) - 403 download(s)