አብይ ምክረ ስላሴ እና ይበሉመሰዋ የደረቅ ፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ የግል ትራንስፖርት የሰበር መዝገብ ቁጥር -257602
ጉዳዩ የግል የሥራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን፣ ክርክሩ በተጀመረበት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ባቀረቡት ክስ ከታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በተጠሪ ድርጅት ተቀጥሮ በወር ብር 31897.00 ደመወዝ እየተከፈላቸዉ የጋራዥና ቴክኒክ ክፍል በመሆን በመስራት ላይ እያሉ ተጠሪ ከህግ ዉጪ የስራ መደብ ለዉጥ በማድረግ ከጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 21721.00 ደመወዝ እየተከፈላቸዉ የጥገና የጥገና ክፍል ከፍተኛ መካኒክ እንዲሰራ ምደባ የሰጣቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ ያላግባብ የተቀነሰባቸዉ ደመወዝ ወደ ነበረበት እንዲመለስ፣ ወደ ነበሩበት የስራ መደብ እንዲመለሱ ይወሰንላቸዉ ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ ….
2061
Documents to download
-
257602(.pdf, 1.03 MB) - 250 download(s)