አቶ ሰንበቶ ዶጊሶ እና ወ/ሮ ብዙነሽ የኋላሸት የሠ/መ/ቁጥር 255911
ጉዳዩ የጋብቻ ፍቺ በንብረት ረገድ የሚያስከትለዉን ዉጤት ለመወሰን የዳኝነት ሥልጣን የሚኖረዉን ፍርድ ቤት የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪ ላይ በመሠረቱት ክስ - በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በዚሁ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 3197 ላይ በቀን 03/02/2015 ዓ.ም በተሰጠው ዉሳኔ ፈርሷል፡፡ በጋብቻ በቆየንበት ወቅት ያፈራነዉ የጋራ ሀብት የሆነ በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ በይዞታ መለያ ቁጥር 000060602004 የተመዘገበ ስፋቱ 203 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የመኖሪያ ቤት እና 3 ክፍል ሰርቪስ ቤት አለን፡፡ እንዲሁም የቤት ዕቃዎች ቁምሳጥን ከነዕቃው፣ፍሪጅ፣የኮካ ሳጥን በቁጥር 2፣የሚሪንዳ ሳጥን በቁጥር 2 የጊዮርጊስ ቢራ ሳጥን አለን፡፡ በመሆኑም ተጠሪ እነዚህን ንብረቶች እንዲያካፍሉኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…
1916
Documents to download
-
255911(.pdf, 1.07 MB) - 293 download(s)