አቶ ተገኝ ደምሴ ወንድአፍራሽ እና ወ/ሮ አየለች ደሳለኝ እንዳሻው የሰበር መ/ቁጥር 248810
ጉዳዩ የንብረት መፋለም ክስን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.13375 በቀን 18/11/2011 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችሎት በመ/ቁ. 04927 በቀን 01/04/2012 ዓ/ም የቀረበውን ይግባኝ ቅሬታ ባለመቀበል የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በትዕዛዝ በማጽናት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል አመልካች ሰኔ 09 ቀን 2015ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ ቅሬታ በማቅረባቸው ነው፡፡
ከሥር ፍርድ ቤቶች የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ በ23/03/2008ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰው የቤት ቁጥር 144 የሆነ በ 2921 ካ.ሜ የመሬት ይዞታ ላይ ያረፈ ሰባት ክፍሎች ያሉት ፎቅ ቤትና ሰርቪስ ቤት ሟች እህታችን በግዥ አግኝተው ሲጠቀሙበት ቆይተው በ1962 ዓ/ም በነበረው የሶማሊያ ጦርነት ወጥተው ስላልተመለሱ ተጠሪ ከወንድሜ ሻምቤል ፈለቀ ደሳለኝ ጋር በመሆን የእህታችንን መጥፋት እና ወራሽነት በ1972 ዓ/ም አሳውጀውን ቤቱ በውርስ ለተጠሪ እና ወንድሜ ከተላለፈ በኃላ፤ የተጠሪ ወንድም በ1988 ዓ/ም በውርስ ያገኙትን የአከራካሪውን ቤት ድርሻ በስጦታ ያስተላለፉልኝን ጨምሮ ከጠቅላላ ይዞታ ውስጥ በ1394 ካ/ሜ ላይ ካርታ በስሜ 11/09/1996 ዓ/ም የተሰራልኝ ሲሆን ቀሪው 1527 ካ/ሜ ይዞታ እና ፎቅ ቤት ወደ ፊት ይሰራልሻል ተብዬ ነበር፤ከዚያ በኋላ ሟች እህቴ ያከራየቻቸው የተከሳሽ ቤተሰቦችከ1969 ዓ/ም ጀምሮ በቤት ውስጥ መኖር ቀጠሉ፤ አመልካች ምንም መብት ሳይኖረው በምዕራብ አቅጣጫ የሚገኙትን አምስት ክፍል ቤቶችን ይዞ በማከራየት፤ ከ2001 ዓ/ም እስከ 2004 ዓ/ም ተለጣፊ ቤቶችን በመስራት እየተጠቀሙ በመሆኑና ቤቱንም ለማስረከብ ፈቃደኛ ስላልሆኑ በሕገ-ወጥ መንገድ የሠሩትን ቤት አፍርሰው የቤት ቁጥር 144 እና ይዞታውን ለቀው እንዲያስረክቡ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…
2468
Documents to download
-
248810(.pdf, 854.77 KB) - 342 download(s)