Login
Federal Supreme Court
Search
  • ዋና ገፅ
  • ስለ ፍርድ ቤቱ
    • የዳኝነት ታሪክና ስርዐት
    • ራዕይ፣ ተልዕኮና የተሰጠ ኃላፊነት
    • ፕሬዝደንት
      • በስራ ላይ ያሉ ፕሬዝደንት
    • ም/ፕሬዝደንት
      • በስራ ላይ ያሉ ም/ፕሬዝደንት
      • የቀድሞ ም/ፕሬዚደንቶች
    • ዳኞች
      • በስራ ላይ ያሉ ዳኞች
      • የቀድሞ ዳኞች
    • አስተዳደር እና ዳይሬክቶሬቶች
  • የፍርድ ቤቱ አገልግሎቶች
    • የሬጂስትራር አገልግሎት
      • የተለያዩ የፍ/ቤት ፎርሞች
    • የፍርድ ቤቱ ዕለታዊ መርሐ-ግብር
    • የጉዳዮች መከታትያ
    • የፍርድ ቤት ሰነዶችን ለመጠየቅ
      • ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን ለመጠየቅ
    • የህግ ድጋፍ
      • የተከላካይ ጠበቆች አገልግሎት
    • የፍርድ ቤት መር አስማሚነት
    • የትርጉም አገልግሎት
  • ኢ-ፋይሊንግ
    • Quick Start Guide
      • መመዝገብ
      • ኢ-መዝገብ መክፈት
    • የአጠቀቃቀም መግለጫ
    • ደንቦችና መመሪያዎች
    • ቅጾች
    • ማስተማሪያዎች እና ማሳያዎች
  • ወደ ፍርድ ቤት ሲሄዱ
    • በፍርድ ቤት ሲገኙ
      • ምን ማየት እና ማድረግ እችላለሁ?
    • የችሎት ውስጥ ሥነሥርዓት
      • ችሎት ስርዓት ደንቦች
    • መረጃ ለወንጀል ተጠርጣሪዎች/ተከሳሾች
    • መረጃ ለፍትሐብሔር ተከራካሪዎች
    • በፍርድ ቤት ራስን ስለመወከል
    • መረጃ- ምስክር ሆነው ለሚቀርቡ
    • መረጃ ለሕግ ባለሙያዎች
    • በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዎች
  • ዲጂታል የሕግ ቤተ መጽሐፍት
    • ዓመታዊ ሪፖርቶች
    • የፍርድ ቤቱ አሁናዊ ሁኔታ
    • የዳኞች ወርሐዊ ጉባዔ
    • በፌደራል መንግሥት የወጡ ሕጎች
    • የተለያዩ ሰነዶች
    • የህትመት ውጤቶች
      • የህግ መጽሄት
      • የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ቅፅ
      • ጋዜጣ
    • ውሳኔዎች
      • ሰበር ውሳኔዎች
      • የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ውሳኔዎች
  • ዜናዎች
    • መግለጫዎች
    • ምስሎችና ሌሎች
      • ፎቶዎች
      • ተንቀሳቃሽ ምስሎች
    • ለመገናኛ ብዙሃን
      • ዜና መግለጫዎች
      • የፍርድ ቤት ውሎ አዘጋገብ ጥቆማዎች
      • ንግግሮች
  • መገናኛ
    • የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
    • የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
    • የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
    • አስተያየት መስጫ
  • የጨረታ-ማስታወቂያ
  • የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
    • ስለ ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
    • የሐራጅ ማስታወቂያ
  • የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት-
    • መጀመሪያ
    • እኛን ለማግኘት
    • አጋር ድርጅቶች
    • አገልግሎቶች
    • አርቲክሎች
    • ዜናዎች
    • ጋለሪ
  • ክፍት የስራ ማስታወቂያ
ረቡዕ ፣ ታህሳስ 1 ቀን 2021
/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ ወ-ሮ ሐመልማል ታመነ ወ-ሮ የምስራች ተካ እና አቶ ክፍሌ ተካ የሰ-መ -ቁ 184335

አመልካች ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 07508 ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችሎት በመዝገብ ቁጥር 07390 ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ፍርድ እና ውሳኔ ማፅናቱ መሠረታዊ የህግ ስህተት ነው በማለት በሰበር ለማሳረም ያቀረቡትን ቅሬታ ለመመርመር መዝገቡ ለችሎት ቀርቧል።ጉዳዩ የውርስ ንብረት እንዲጣራ የቀረበ ክርክር ሆኖ ክርክሩ በተጀመረበት የሼይ ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በከሳኝነት ፣ በሰበር ክርክሩ የሌሉት አቶ ፍቃዱ ተካ በተከሳሽነት እና አመልካች እና ሌሎች በሰበር ክርክሩ ተካፋይ ያልሆኑት 3 ሰዎች በጣልቃ ገብነት ተከራክረዋል። 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት የውርስ ይጣራ አቤቱታ ከሥር ተከሳሽ ጋር ከሟች አቶ ተካ ከበደ የሚወለዱ መሆኑንና አባታቸው ጳጉሜ 1 ቀን 2009 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ገልጸው በህይወት በነበሩበት ወቅት በሚዛን ከተማ ህብረት ቀበሌ ኮንዶሚንዬም ፊት ለፊት ከመንገድ በታች ያለው አንድ ክፍል ቤት ከይዞታው ጭምር እንዲሁም ሌሎች በሟቹ የተፈሩ ናቸው የሚሉትን ንብረቶችን በመዘርዘር የውርስ ንብረቶቹን ሌሎች በእጃቸው ይዘው የሚገለገሉበት መሆኑን ገልፀው ድርሻቸውን ማግኘት እንዲችሉ የውርስ አጣሪ ተሹሞ የውርስ ሀብቱ እንዲጣራ ፣ ወራሾች እንዲለዩ እና ንብረቶቹ በአጣሪው እንድተዳደሩ እንድወሰን አመልክቷዋል። የሥር ተከሳሽ ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ መሆኑን መዝገቡ የሚያስረዳ ሲሆን በአማራጭ በፍሬ ነገሩ ላይ ባቀረቡት መልስም በክሱ ውስጥ መብት እና ጥቅም ያላቸው አመልካች እና ሌሎች ሰዎች ስላሉ በፍርድ ቤቱ ጥር ወደ ክርክሩ እንዲገቡ ፤ የውርስ አጣሪ እንዲሾም ፤ የውርስ ንብረቱ የወራሾች የጋራ ሆኖ በሟች በመታሰቢያነት በቅርስነት እንዲቆይ ፤ ለሟች ተስካር ፣ የሙት ዓመት እና ሌሎች ወጪዎች እንድሁም ዕዳም ካለ እንድጣራ ጠይቋል። አመልካች እና ሌሎች ከውርስ ሀብቱ መብት አለቸው የተባሉትን አራት ሰዎች በፍርድ ቤቱ ጥሪ ወደ ክርክሩ ገብተው ከሥር ተከሳሽ ጋር የሚመሳሰል መልስ መስጠታቸውን ፍርድ ቤቱ  መዝግቧል። ፍርድ ቤቱ የውርስ አጣሪ የሾመ ቢሆንም የሟች ውርስ ሀብት በአግባቡ አልተጣራም በማለት ሪፖርቱ ውድቅ በማድረግ ግራ ቀኙ ወደ ክርክሩ እንድገቡ አድርጓል። የሥር ተከሳሽ በሚዛን ከተማ ህብረት ቀበሌ ኮንዶሚንየም ሰፈር ያለው ቤት በሟች ስም አለመመዝገቡ ፣ የሟች ቀለበቶች በእሱ እጅ አለመኖራቸውን ፣ ለሟች አርባ እና የተለያዩ ወጪዎች ተጣርተው ቀርበው ክፍፍል እንድደረግ ጠይቋል። ጣልቃ ገቢዎችም ተመሳሳይ ክርክር ማቅረባቸው በፍርዱ ላይ የተመላከተ ሲሆን የሥር ከሳሽም በጽሁፍ ክርክራቸው የጠየቁትን ዳኝነት በማንሳት መከራከራቸው ተመላክቷል።……….

Previous Article አቶ ግደይ ገ-ጻድቃን ገ-ማርያም እና ወ-ሮ ክንድሀፍቲ ኢታይ የሰ-መ-ቁ 179589
Next Article እነ ወ-ሮ ፈይዛ ከማል አወል፣አቶ አብዲ አህመድ መሀመድ እና አቶ ካህሳይ ተስፋዝጊ የሰ-መ-ቁ 184601
Print
16584

Documents to download

  • እነ ወ-ሮ ሐመልማል ታመነ ወ-ሮ የምስራች ተካ እና አቶ ክፍሌ ተካ የሰ-መ -ቁ 184335(.pdf, 516.95 KB) - 1252 download(s)

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    መገናኛ
  • ስልክ : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • ፋክስ : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • ኢሜል : fscpublicrelation@gmail.com
  • አድራሻ ፡ 6 ኪሎ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ፈጣን አገናኝ
  • ስለፍርድ ቤቱ 
  • ኢ-ፋይሊንግ
  • የቀን መቁጠሪያ
  • ዜና መግለጫዎች
  • የጉዳዮች መከታተያ
  • በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዎች
    ያግኙን
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright 2026 by Federal Supreme Court
Powered By Bsquare IT Solutions