Login
Federal Supreme Court
Search
  • ዋና ገፅ
  • ስለ ፍርድ ቤቱ
    • የዳኝነት ታሪክና ስርዐት
    • ራዕይ፣ ተልዕኮና የተሰጠ ኃላፊነት
    • ፕሬዝደንት
      • በስራ ላይ ያሉ ፕሬዝደንት
    • ም/ፕሬዝደንት
      • በስራ ላይ ያሉ ም/ፕሬዝደንት
      • የቀድሞ ም/ፕሬዚደንቶች
    • ዳኞች
      • በስራ ላይ ያሉ ዳኞች
      • የቀድሞ ዳኞች
    • አስተዳደር እና ዳይሬክቶሬቶች
  • የፍርድ ቤቱ አገልግሎቶች
    • የሬጂስትራር አገልግሎት
      • የተለያዩ የፍ/ቤት ፎርሞች
    • የፍርድ ቤቱ ዕለታዊ መርሐ-ግብር
    • የጉዳዮች መከታትያ
    • የፍርድ ቤት ሰነዶችን ለመጠየቅ
      • ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን ለመጠየቅ
    • የህግ ድጋፍ
      • የተከላካይ ጠበቆች አገልግሎት
    • የፍርድ ቤት መር አስማሚነት
    • የትርጉም አገልግሎት
  • ኢ-ፋይሊንግ
    • Quick Start Guide
      • መመዝገብ
      • ኢ-መዝገብ መክፈት
    • የአጠቀቃቀም መግለጫ
    • ደንቦችና መመሪያዎች
    • ቅጾች
    • ማስተማሪያዎች እና ማሳያዎች
  • ወደ ፍርድ ቤት ሲሄዱ
    • በፍርድ ቤት ሲገኙ
      • ምን ማየት እና ማድረግ እችላለሁ?
    • የችሎት ውስጥ ሥነሥርዓት
      • ችሎት ስርዓት ደንቦች
    • መረጃ ለወንጀል ተጠርጣሪዎች/ተከሳሾች
    • መረጃ ለፍትሐብሔር ተከራካሪዎች
    • በፍርድ ቤት ራስን ስለመወከል
    • መረጃ- ምስክር ሆነው ለሚቀርቡ
    • መረጃ ለሕግ ባለሙያዎች
    • በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዎች
  • ዲጂታል የሕግ ቤተ መጽሐፍት
    • ዓመታዊ ሪፖርቶች
    • የፍርድ ቤቱ አሁናዊ ሁኔታ
    • የዳኞች ወርሐዊ ጉባዔ
    • በፌደራል መንግሥት የወጡ ሕጎች
    • የተለያዩ ሰነዶች
    • የህትመት ውጤቶች
      • የህግ መጽሄት
      • የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ቅፅ
      • ጋዜጣ
    • ውሳኔዎች
      • ሰበር ውሳኔዎች
      • የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ውሳኔዎች
  • ዜናዎች
    • መግለጫዎች
    • ምስሎችና ሌሎች
      • ፎቶዎች
      • ተንቀሳቃሽ ምስሎች
    • ለመገናኛ ብዙሃን
      • ዜና መግለጫዎች
      • የፍርድ ቤት ውሎ አዘጋገብ ጥቆማዎች
      • ንግግሮች
  • መገናኛ
    • የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
    • የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
    • የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
    • አስተያየት መስጫ
  • የጨረታ-ማስታወቂያ
  • የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
    • ስለ ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
    • የሐራጅ ማስታወቂያ
  • የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት-
    • መጀመሪያ
    • እኛን ለማግኘት
    • አጋር ድርጅቶች
    • አገልግሎቶች
    • አርቲክሎች
    • ዜናዎች
    • ጋለሪ
  • ክፍት የስራ ማስታወቂያ
ቅዳሜ ፣ ታህሳስ 4 ቀን 2021
/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ ወ-ሮ ፈይዛ ከማል አወል፣አቶ አብዲ አህመድ መሀመድ እና አቶ ካህሳይ ተስፋዝጊ የሰ-መ-ቁ 184601

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ን/ስ/ላ/ምድብ በኮ.መ.ቁ 88409 በ16/2/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ.መ.ቁ 222352 በ19/11/11ዓ.ም በሰጠው ብይን/ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት በ11/2/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የን/ስ/ላ/ ምድብ 4ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በ1ኛ ተጠሪ ላይ ጋብቻቸው በፍ/ቤት በ23/4/07ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ በፍቺ መፍረሱን ተከትሎ ባቀረቡት የጋራ ንብረት ክፍፍል ክስ አከራካሪውን የሰ.ቁ ኮድ A-13872 ያሪስ መኪና ዋጋው ብር 550‚000 የሚያወጣ እና ሌሎች ንብረቶችን የእቁብ ገንዘብን ጨምሮ በመዘርዘር ንብረቶቹ የጋራችን ስለሆኑ እኩል እንድንካፈል እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት መልስ በጋብቻ ውስጥ እያለን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቀበሌ 13 የቤት ቁጥር 069 በአቶ መሃመድ ይማም ዳኝነት በአቶ እንድሪስ አለሙ ጸሀፊነት በአቶ ወንድሜነህ አለሙ ይሰበሰብ የነበረው እቁብ በ29/4/04ዓ.ም ደርሶኝ ለትዳራችን ጥቅም ያዋልኩት ሲሆን፤ ይህን እቁብ መክፈል ባለመቻሌ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ፍ/ብሄር ችሎት በመ.ቁ 38976 ክስ ቀርቦብኝ ገንዘቡን እንድከፍል በ30/4/05ዓ.ም ተወስኖብኝ ከነወጪና ኪሳራ ብር 149‚365.95 እንድከፍል በመገደዴ አመልካች ያካፍለኝ በማለት ያቀረበችውን የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን መኪና ሸጬ እዳውን ከከፈልኩኝ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ለትዳር ጥቅም ስለዋልኩት ጥያቄው አግባብ አይደለም በማለት ተከራክረው እንዲሁም በሌሎች ንብረቶችም ላይ መልስ የሰጡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራቀኙን በቃል ካከራከረ በኋላ ግራቀኙ በጋብቻ እያሉ የጋራቸው የሆነ እዳ ነበር ወይስ አልነበረም? አከራካሪውን የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን መኪና ግራቀኙ በትዳር እያሉ ተሸጦ ለጋራ እዳ ክፍያ እና ለትዳር ጥቅም ውሏል ወይንስ አልዋለም? የሚለውን እና ሌሎች ንብረቶችን በተመለከተ የተለያዩ ጭብጦችን በመያዝ፤ አከራካሪውን መኪና በተመለከተ ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ትእዛዝ በመስጠት ምላሽ ከቀረበለት በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የጋራ እዳን በተመለከተ 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በጋብቻ እያለን ለደረሰብኝ እዳ መክፈል ባለመቻሌ በፌ/መ/ደ/ፍቤት አራዳ ምድብ ችሎት በመ.ቁ 38976 በ30/4/05ዓ.ም ከወጪና ኪሳራ ጭምር ብር 149‚365.95 እንድከፍል ተወስኗል ያሉትን በተመለከተ እዳው የመጣው ባልና ሚስት በጋብቻ አብሮ እያሉ ስለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ እዳው የጋራቸው ነው በማለት ከወሰነ በኋላ ከላይ የተገለጸውን ገንዘብ እንዲከፈል የተወሰነው በ30/4/05ዓ.ም በመሆኑ ለዚህ እዳ መኪና ተሸጠ የተባለው በ2007ዓ.ም ነው፤ 1ኛ ተጠሪ መኪናው በእዳ ተይዞ ተገዶ ለመሸጡ ሆነ ገንዘቡ ከመኪና ሽያጭ ለመከፈሉ ምንም ማስረጃ አላቀረበም፤ እዳው ከተከፈለም እዳው የመጣው በጋብቻ እያሉ በመሆኑ በጋብቻ አብረው እያሉ እንደተከፈለ የሚቆጠር በመሆኑ መኪና ተሸጦ ተከፈለ በማለት 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክር ባለመቀበል፤ የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን ያሪስ የቤት መኪና አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በጋብቻ እያሉ ያልተሸጠ እና ለጋራ እዳም ሆነ ለትዳር ጥቅም ያለመዋሉ ከመረጋገጡም በላይ 1ኛ ተጠሪ ተሸጧል ሲል ቢከራከርም መኪናው ከመሸጡ በፊት በፍ/ቤት በ13/2/07ዓ.ም የታገደ መሆኑን 1ኛ ተጠሪም የሚያውቀው በመሆኑ፤ ለመሸጡ የንፋስ ስልክ ላፍቶ የመንገድና ትራንስፖርት የሰጠው መረጃ ታማኝነት የሌለው እና ውድቅ የተደረገ በመሆኑ ቢሸጥ እንኳን አስቀድሞ በፍ/ቤቱ የታገደ በመሆኑ ተገቢነት የለውም በማለት፤ በ1ኛ ተጠሪ እጅ የሚገኘው የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን ያሪስ የቤት መኪና የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረታቸው ነው በማለት፤ ክፍፍሉን በተመለከተ ከተስማሙ አንዱ ለሌላው ግምቱን በመስጠት ያስቀረው፤ በዚህ ካልተስማሙ መኪናው በሀራጅ ተሸጦ ገንዘቡን እኩል እንዲካፈሉ በማለት በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 90 መሰረት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ሌሎች ንብረቶችን በተመለከተም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡………….

Previous Article እነ ወ-ሮ ሐመልማል ታመነ ወ-ሮ የምስራች ተካ እና አቶ ክፍሌ ተካ የሰ-መ -ቁ 184335
Next Article ህፃን ሒዳያ አማን መሀመድ እና አመተበል መሃመድ የሰ-መ-ቁ 185175
Print
16766

Documents to download

  • እነ ወ-ሮ ፈይዛ ከማል አወል፣አቶ አብዲ አህመድ መሀመድ እና አቶ ካህሳይ ተስፋዝጊ የሰ-መ-ቁ 184601(.pdf, 522.12 KB) - 1155 download(s)

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    መገናኛ
  • ስልክ : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • ፋክስ : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • ኢሜል : fscpublicrelation@gmail.com
  • አድራሻ ፡ 6 ኪሎ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ፈጣን አገናኝ
  • ስለፍርድ ቤቱ 
  • ኢ-ፋይሊንግ
  • የቀን መቁጠሪያ
  • ዜና መግለጫዎች
  • የጉዳዮች መከታተያ
  • በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዎች
    ያግኙን
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright 2026 by Federal Supreme Court
Powered By Bsquare IT Solutions