ወ/ሮ አገሪቱ በዛ እና አቶ በላይ በዛ የሠ/መ/ቁጥር 253704
የቀረበዉ ክስ ይዘት የሰበር አመልካቾች እና ተጠሪዎች የአንድ አባት እና እናት ልጆች ስንሆን ሟች እናታችን አደሌ ገላዉ በህወት ሳለች በ2002 ዓ/ም በዳዉንት ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ቀርባ የመሬት ይዞታዋን ተናዛልን ወራሽነታችንንም አስወስነናል የሰበር አመልካቾች ይዘዉ ስለሚገኙ ድርሻችንን እንዲያካፍሉን ይወሰንልን የሚል ነዉ፡፡ የሰበር አመልካቾች የሰጡት መልስ ይዘትም ክሱ በይርጋ ቀሪ ነዉ፡፡ ሟች እናታችን በ2002 ዓ/ም ለግራ ቀኛችን ያደረገችዉን ኑዛዜ በ2004 ዓ/ም አንስታ ለእኛ በኑዛዜ አስተላልፋለች ፡፡ በኑዛዜዉ መሰረትም ድርሻችንን ተካፍለን በድርሻችን ላይ ቤት ሰርተን እየኖርን የምንገኝ ስለሆነ የመናካፈላቸዉ የዉርስ ሀብት የለም የሚል ነዉ ፡፡ ጉዳዩ በዚህ መልክ የቀረበለት የዳዉንት ወረዳ ፍርድ ሟች እናታቸዉ በ2002 ዓ/ም ለተጠሪ ጭምር ተናዘዉ የነበረ ቢሆነም በ2004 ዓ/ም ለሰበር አመልካቾች የተናዘዙ ስለሆነ የ2002 ዓም ኑዛዜ ቀሪ ስለሆነ መብት ያላቸዉ የአሁን አመልካቾች ናቸዉ ሲል ወስኗል ፡፡ተጠሪ በዉሳኔዉ ቅር ተሰኝተዉ ጉዳዩን በይግባኝ ለሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወረዳዉ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ስህተት የለበትም በማለት ቅሬታዉን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337 መሰረት ሰርዞታል፡፡መልካም ንባብ…
1855
Documents to download
-
253704(.pdf, 849.53 KB) - 263 download(s)