ወ/ሮ የሺ ሽብሩ እና አቶ ከበደ ድንቁ የሰበር መ/ቁ255586
ጉዳዩ የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች የጋብቻ ፍቺን ተከትሎ በቀረበው የንብረት ክርክር ስምምነት ባልተደረሰባቸው ንብረቶች ላይ የቀረበ ዳኝነትን የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ ተጀመረው በሄጦሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ በሌላ በኩል ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡አመልካች ባቀረቡት ክስ የአመልካች እና ተጠሪ ጋብቻ ፍቺ ውሳኔን ተከትሎ በተደረገው የንብረት ክፍፍል መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረግነው የዕርቅ ስምምነት የተወሰኑትን ንብረቶች የተከፋፈልን ሲሆን በስምምነት ያልተከፈልነው በምስራቅ መንገድ፣በምዕራብ ገመቹ ተሾመ፣በሰሜን ብርብርሳ ጅማ፣በደቡብ የሺ ጎሹ የሚዋስኑትን ባለ 60 ቆርቆሮ የመኖሪያ ቤት፣13 ሉክ ቆርቆሮ ኩሽና ቤት፣22 ቆርቆሮ የዕቃ ማጠራቀሚያ፣20 ሉክ ቆርቆሮ ቤተሰብ የሚገቡበት፣ ሶስት ሳር ቤት፣አንድ የከብቶች የሚገቡበት በረት ሌሎች ንብረቶችንም በዝርዝር በመጥቀስ ተጠሪ እንዲካፍለኝ የሚል ነው፡፡ተጠሪም በሰጡት መልስ የክርክር መነሻ የሆነው ንብረት በስምምነቱ ወቅት የእኔ እንደሆነ በተደረገው ዕርቅ ስምምነት የተደረሰበት በመሆኑ የቀረበው ክስ ውድቅ እንዲደረግ በሚል ተከራክረዋል፡፡መልካም ንባብ…
3938
Documents to download
-
255586(.pdf, 865.45 KB) - 467 download(s)