ወ/ሮ ድላይ አማረ እና እነ ወ/ሮ ለታይ ደሳለኝ የሰበር መ/ቁ 193894
ጉዳዩ አመጣጥ ከመዝገቡ እንደተገነዝበነዉ ክርክሩ የእርሻ መሬት ይዞታ የሚመለከት ሲሆን በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ አመልካች ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሽ በመሆን ተከራከረዋል፡፡ አመልካች በሳምረ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 04501 በቀን 19/03/2012 ባቀረበችው ክስ የሳምረ ከተማ ነዋሪ ሲሆን በ1979 ዓ.ም የተሰጠኝን በዓምዲ ወያነ ደብረሓይላ የሚገኝ የእርሻ መሬት ይዞታዬን ተጠሪዎች ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የያዙት ሲሆን 1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደብረገነት ተብሎ በሚታወቅ ቦታ የካርታ ቁጥር 10701010-01881 የሆነ እንዲሁም ቀብቀብ በተባለ ቦታ የካርታ ቁጥር 13784 የሆነ ይዞታ፤ 2ኛ ተጠሪ በበኩሏ ሓዱሽ ቀኒ በተባለ ቦታ የካርታ ቁጥር 00827 አዋሳኛቸው በክሱ የተጠቀሰውን ይዞታዬን ይዘውብኛል፤ የእድሜ ባለፀጋ በመሆኔ በመሬት የመጠቀም መብቴን ልነጠቅ አይገባም ፤በ27/13/2005ዓ.ም የቀበሌው መሬት አስተዳደር መሬቴን እንዳልቀማ ወስኗል፡፡በመሆኑም ይዞታዬን ለቀው እንዲያስረክቡኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀች መሆኑን፤ተጠሪዎች በ27/07/2011ዓ.ም በሰጡት መልስ የመሬት እደላ የተካሄደው በ1974 ዓ.ም በህንፃሎ ወረዳ ደብረኃይላ ቀበሌ መገንዓ በተባለ መንደር እንጂ በ1979 አይደለም፤አመልካች በወቅቱ በቦታው አልነበሩም፤መሬቱ የተሰጣቸው ከደርግ ሰፈራ በ1984 ዓ.ም ሲመለሱ ነው፤ መሬቱ የተሰጣቸው በዓምዲ ወያነ ደብረኃይላ ቀበሌ መገንዓ መንደር ነዋሪ ሆነው ነው፤ወደ ሳምረ ከተማ የሄዱትም በ2000 ዓ.ም ሲሆን የሄዱት ጧሪ አጥተው እንዲጦሩ ሳይሆን ጠላ ሸጠው ለመተዳደር ነው ፤ቀበሌው መሬታቸውን በ2008 እንዲነጠቁ በማድረግ ለተጠሪዎች በሽግሽግ ዕጣ ወጥቶ ተሰጥቶናል፤አመልካች ጤነኛና ሰርተው መኖር የሚችሉ ናቸው ክሱ ውድቅ ይደረግልን በማለት መከራከራቸዉን መዝገቡ ያሣያል፡፡መልካም ንባብ……
1698
Documents to download
-
193894(.pdf, 874.08 KB) - 213 download(s)