ወ/ሮ ፋንቱ ዘነበ (2ሰዎች) እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእንጦጦ ስብሐት ቅድስት ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን መ.ቁ 246386
የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ በመሆን አመልካቾች 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሽ በመሆን እንዲሁም በዚህ ክርክር ተካፋይ ያልሆኑት እነ ሳልሳይ ኤፍሬም ጌታቸው 4 ሰዎች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ፣ 3ኛ፣ 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ተጠሪ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበችው የተሻሻለ ክስ የአባ ኃይለስላሴ መገኖ ርስት እና ንብረት የሆነው አንድ ጋሻ ይዞታ ሰኔ 17 ቀን 1948 ዓ.ም በተደረገ ግልጽ ኑዛዜ የተሰጣት መሆኑን ኑዛዜው በከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 169/55 ግንቦት 13 ቀን 1955 ዓ.ም መጽደቁን እና ከሳሽ ይዞታውን ተረክባ ስታስተዳድር የቆየች መሆኑን፤ ከአንድ ጋሻ መሬት ላይ 1192 ካ.ሜ ይዞታ ቀንሳ ለአገልጋይ ካህናት ደመወዝ መክፈያ ይሆን ዘንድ የ1ኛ አመልካች ባለቤት ለነበሩት ለአቶ ኤፍሬም ጌታነህ በወር ብር 30 (ሰላሳ) ሂሳብ ለአምስት ዓመታት አከራይታ የኪራይ ውሉ እስከ 1967 ዓ.ም እየተራዘመ መቆየቱን፤ ይዞታው ያልተወረሰ እና የግል ቤቴ ነው በማለት አቶ ኤፍሬም ጌታነህ በ2004 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ እንደ ቅደም ተከተላቸው የስር 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች የነበሩት ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር እና ጉለሌ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር የቤት ቁጥር 815(ለ) በሚል በአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ስም ተመዝግቦ ስም እንዲዞር ማድረጋቸውን፤ ይህንኑ ይዞታ የአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ወኪልና የስር 4ኛ ተከሳሽ(2ኛ አመልካች) የቦርድ ሰብሳቢ በሆኑት አቶ መኮንን አያሌው እና የተጠሪ ፀሀፊ ዲያቆን ተስፋሚካኤል ታደሰ አመልካችነት ይዞታው ወደ አቶ ኤፍሬም ጌታነህ እንዲተላለፍ በመጠየቁ ህዳር 17 ቀን 2005ዓ.ም ቁጥሩ 22/69/28322/00 የሆነ ካርታ በአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ስም ተዘጋጅቶ ተሰጥቷል፡፡ ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም በተደረገ በሽያጭ ውል ለ2ኛ አመልካች(ስር 4ኛ ተከሳሽ) ተላልፏል፡፡ የተጠሪ ይዞታ ከህግ ውጪ የተላለፈ በመሆኑ የስር 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች የይዞታውን ባለቤት በአግባቡ ሳያጣሩ በአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ስም በ17/3/2005ዓ.ም አዘጋጅተው የሰጡትን ካርታ እንዲሰርዙ፤ በሟች አቶ ኤፍሬም ጌታነህ እና በስር 4ኛ ተከሳሽ(2ኛ አመልካች) መካከል የተደረገው በ15/12/2005ዓ.ም የተደረገው ውል እንዲሰረዝ፤ የስር 5ኛ ተከሳሽ አለአግባብ በሰጠው መረጃ መሰረት ለስር 4ኛ ተከሳሽ(2ኛ አመልካች) የተሰጠው ካርታ እንዲሰረዝ፤ በምትኩ የስር 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ለይዞታው ለተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰጡ፤ በይዞታው ላይ ያለን ንብረት 2ኛ አመልካች አንስቶ ይዞታውን ለተጠሪ እንዲያስረክብ እንዲወሰን በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፡፡ ማስረጃዎችንም አያይዛለች፡፡ነው፡፡መልካም ንባብ…
2840
Documents to download
-
246386(.pdf, 896.3 KB) - 405 download(s)