ፀሐይ ኢንሹራስ አክሲዮን ማህበር እና ልጉዲ እርሻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁ 261799
ጉዳዩ የንብረት ጉዳት ካሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ አመልካች በቀን 04/09/2015 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ ባቀረቡት ክስ የመድን ዋስትና ሽፋን የተሰጠው ንብረትነቱ በተጠሪ ስም የተመዘገበ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ ኢት 3-77600 እና ኢት 3-23463 ዋና እና ተሳቢ ተሽከርካሪ በቤንሻንጉል ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ሆርሶ ቀበሌ ልዩ ቦታው ማንጁል ቡሾ በተባለ ቦታ ማንነታቸው ያልታወቁ ሽፍቶች ባደረሱት ጥቃት ከነተሳቢውና ከጫነው ጭነት ጋር ሙሉ ለሙሉ ሊወድም ችሏል፡፡ የአደጋው መንስኤ በመደበኛ የመድን ውሉ የተገለለ ቢሆንም ከሳሽ በተጨማሪ አረቦን ክፍያ የባንዲት፣ የሽፍታ እና ጎሬላ የመድን ሽፋን ለተሽከርካሪው ከነተሳቢው የተገባለት(sum insured) ብር 4,500,000.00(አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) ነው፡፡ ተጠሪ አደጋውን በጊዜው ከማሳወቅ ጀምሮ ተገቢውን የኢንሹራንስ ሂደት ያሟላ ቢሆንም አመልካች አደጋው የመድን ሽፋን የለውም በሚል የከሳሽን የካሳ ጥያቄ ውድቅ ያደረገ በመሆኑ ብር 4,500,000.00 (አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) ካሳ መክፈል ከሚገባው ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ፣ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…
2411
Documents to download
-
261799(.pdf, 1.07 MB) - 317 download(s)