ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ እና አቶ ጣሂር ሙስጠፋ /6 ሰዎች/ሰ.መ.ቁ 258301
ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ የቀረበው አመልካች የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት በመዝገብ ቁጥር 296546 በ25/4/2016ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ20/5/2016ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረበ ነው፡፡
የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪዎች(የስር ከ20ኛ-25ኛ ከሳሾች) በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ( ተጠሪዎች በአመልካች ላይ በስር ፍርድቤት ያቀረቡት ክስ ሌሎች በዚህ የሰበር ክርክሩ ላይ የሌሉ የስር ከ1ኛ እስከ 19ኛ ከሳሾች በሌላ መዝገብ ካቀረቡት ክስ ጋር ተጣምሮ የታየ) በአመልካች ድርጅት በተለያየ የስራ መደብ በቋሚነት እስከ 23/5/2015ዓ.ም እና 23/6/2015ዓ.ም ስናገለግል ቆይተናል፡፡ ሆኖም አመልካች ባስጠናው የደመወዝ ስኬል ጥናት መሰረት የተወሰኑ የስራ መደቦች የሚያስፈልገው የሰው ሀይል ብዛት በመቀነሱ እንዲሁም ሌሎች ደግሞ በመታጠፋቸው በሚል ምክንያት በአዋጁ አንቀጽ 28 መሰረት ከአመልካች ጋር የስራ ውል የተቋረጠ መሆኑን በመግለጽ ከስራ አሰናብቶናል፡፡መልካም ንባብ ….
2294
Documents to download
-
258301(.pdf, 845.65 KB) - 270 download(s)