የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት በቀን 02/11/2017 ዓ.ም አቅርቧል፡፡
የዳሰሳ ጥናቱ ዓላማ በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የእውቀት፣ ክህሎት እና ሙያዊ አመለካከት ክፍተቶች ካሉ በዳሰሳ ጥናት በመለየት ለዳኞች የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ለመስጠት እና የዳኞችን የስልጠና ፍላጎት ለመለየት ነው፡፡