የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2019 በጀት ዓመት መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ዛሬ ተከናውኗል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢያለ፣ የዳኝነት ሥራ ዘመኑ በሦስቱም የፌደራል ፍርድ ቤቶች በይፋ መጀመሩን አብስረዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ባለፈው የአምስት ዓመት (2014–2018) ስትራቴጂክ ዕቅድ ዘመን ውጤታማ አፈጻጸም የተመዘገበበት እንደነበር ገልጸዋል።